#FastMereja I የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ሽያጭ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በማስጀመር የአክሲዮን ሽያጩን እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡
በመቀጠልም ውጤቱን ለሚመለከተው የመንግስት አካል እና ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በማቅረብ እና በመገምገም በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሽያጭ ቀነ-ገደቡን በማራዘም እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማለትም ለ121 ቀናት (የዕረፍትና የበዓል ቀናትን ጨምሮ) በዲጂታል መንገድ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት የተከናወነው የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ ውጤት በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት አካላት ተገምግሞ እንዲሁም በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታይቶ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች በስፋት በመሳተፍ በአጠቃላይ ከ47,377 ዜጎች ከ10.7 ሚሊዮን የኢትዮ ቴሌኮም መደበኛ አክሲዮኖች የግዢ በዲጂታል መንገድ በማከናወን ብር 3.2 ቢሊየን የሚጠጋ ሀብት ለማሰባሰብ ተችሏል፡፡
በቀጣይ ከእያንዳንዱ አመልካች ጋር በሚኖር የቀጥታ ግንኙነት ያልተሟሉ መረጃዎችን የማሟላት ተግባር በማከናወን የኢትዮ ቴሌኮም ባለቤት የሚሆኑበት ማረጋገጫ የመስጠት ስራ ይከናወናል፡፡
የተሸጡ አክሲዮኖች ድልድል በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የማጽደቅ ሂደት ከተከናወነ በኋላ ውጤቱ በይፋ ይገለፃል። የተደለደሉ አክሲዮኖች በማዕከላዊ የሰነዶች ሙዓለ ነዋዮች ግምጃ ቤት ይመዘገባሉ፤ ይህም ሂደት እስኪጠናቀቅ ኩባንያው መረጃዎችን ለባለአክሲዮኖች ደረጃ በደረጃ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ባለድርሻ የሚሆኑ ባለአክስዮኖች በቀጣይ በኢትዮጵያ የሰነዶች ሙዓለ ነዋዮች ገበያ አክሲዮናቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተቋሙ በገበያው እንዲመዘገብ ቀጣይ ስራዎች የሚከናወኑ ሲሆን ቀሪ አክስዮኖች በተመለከተ ዝርዝር የሽያጭ ሂደቱን በቀጣይ የሚገለፅ ይሆናል።
አሁን አክሲዮን የገዙ ባለድርሻዎችን መብት ባስጠበቀ መልኩ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ይሁንታ በማግኘት በድጋሚ ለገበያ የሚቀርቡ መሆኑ ተነግሯል።

5 comments
ገዝተን ነበር ግን ወፍ 😁
እርዳታ ሰጡ ቢባል ይሻላል
እኔ ነኝ የረሁት😀
ye ethiopia hzb eko 130 million nw,,,,silezy afetsatsemu ejig betam zqitegna w
ምን ያክሉ ደሞ በቴሌብር ተበድሮ ያልመለሰ ቢገለጸልን