banner

በኢትዮጵያ የመጀመርያው የሀይኪንግ ውድድር ሊካሄድ ነው!

#FastMereja I ላለፉት 10 አመታት በአካል ብቃት፣ ስርዓተ ምግብ፣ በሕይወት ክህሎት በውፍረት እና ከውፍረት ጋር በተያያዘ ለሚቸገሩ ወገኖች ሳይንሳዊ በሆነ ስልጠና በመስጠት የሚታወቀው ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሀይኪንግ ውድድር እና ፌስቲቫል ሊያካሂድ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ታላቁ የተራራ ላይ ውድድር እና ፌስቲቫል የፊታችን ሚያዝያ 23/2017 ዓም መነሻውን እንጦጦ ቁስቋም ማርያም መዳረሻውን ደግሞ እንጦጦ ፓርክ በማድረግ እንደሚከናወን በመግለጫው ላይ ተነግሯል፡፡

ውድድሩ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ከ10ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮች ቻሌንጆች ፤ ፌስቲቫል፣ የጫካ ሲኒማና ሌሎች ፕሮግራሞች ይከናወናሉ።

ቲሸርቱን ከቴሌብር ላይ በ500 ብር መግዛት እንደሚቻል ተነግሯል።





1 comment

ሄዋን ጓል እድብቲ April 25, 2025 - 4:11 pm

follow ላደረገኝ 10 star እልክለታለው

Reply

Leave a Comment