banner

የበልሻ ፋውንዴሽን በይፋ ስራ መጀመሩ ተበሰረ

#FastMereja I የበልሻ ፋውንደለሽን ዛሬ ሚያዚያ 18 ቀን 2017 ዓም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች፣ በካንሰር ላይ የሚሰሩ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የበልሻ ፋውንዴሽን የቦርድ አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

የበልሻ ፋውንዴሽን ስያሜውን ያገኘው ነዋሪነታቸውን በአሜሪካን አገር አድርገው በነበሩትና በበጎ አድራጎት ሥራቸው በሚታወቁት ወይዘሮ በለጠች ሞላ (በልሻ) ሲሆን እኚህ በጎ አድራጊ ቅንና መልካም ሴት ሕይወታቸውን ያጡት በካንሰር ህመም በመሆኑ በእሳቸው ሕልፈት ሐዘንና ቁጭት ያደረባቸው ባለቤታቸው፣ ቤተሰባቸውና ወዳጆቻቸው የበልሻን የበጎ አድራጎት ሥራ ለማስቀጠል እና እሷን የነጠቃቸውን ካንሰርን ለመዋጋት በማሰባቸው ይህ የበጎ አድራጎት ድርጅት እንዲመሠረት ምክንያት ሆኗል፡፡

የበልሻ ፋውንዴሽን ዓለማ የካንሰር በሽታን የመከላከል ሥራ መሥራት፣ ህሙማን የህክምና አገልግሎት እና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፤ በካንሰር እና በሌሎች ምክንያቶች ወላጅ አልባ የሆኑ እና ለችግር የተጋለጡ ህጻናትን መደገፍ እና መንከባከብ እንዲሁም አረጋውያን እና አቅመ ደካማዎችን መደገፍ እና መንከባከብ ዓለማ አድርጎ እንደተመሰረተ የፋውንዴሽኑ መስራች እና ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ መብራቱ ተናግሯል።

የበልሻ ፋውንዴሽን አገር በቀል ድርጅት ሆኖ በአዋጅ ቁጥር1113/2011 መሠረት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በመዝገብ ቁጥር 7416 ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት ያለውና በካንሰር ላይ ለመሥራት የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡





Leave a Comment