0
#FastMereja I የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የግንባታ ስራን የሚሳልጥ Enterprise resource planning (ERP) የተሰኘ የቴክኖሎጂ ውጤት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን በተገኙበት ስራ ላይ ማዋሉን ገለጸ።
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ባደረጉት ንግግር የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልልቅ ስራዎች መስራቱን ገልጸው የክልሉ መንግስት እየሰራበት ያለውን ዘመናዊ የከተማ ግንባታ ውስጥ ተቋሙ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው በትልቅ ጉልበት እና የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መስራት እንዳለበት ተናግሯል።
ተቋሙ ወደ ኢንዱስትሪ በሚደረገውን ሽግግር ውስጥ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል።




