banner

በኢትዮጵያ የመጀመርያው የሀይኪንግ ውድድር ተካሄደ

#FastMereja I ላለፉት 10 አመታት በአካል ብቃት፣ ስርዓተ ምግብ፣ በሕይወት ክህሎት በውፍረት እና ከውፍረት ጋር በተያያዘ ለሚቸገሩ ወገኖች ሳይንሳዊ በሆነ ስልጠና በመስጠት የሚታወቀው ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት ስልጠናዎች በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሀይኪንግ ውድድር እና ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት በእንጦጦ ፓርክ አካሂዷል።

ታላቁ የተራራ ላይ ውድድር እና ፌስቲቫል መነሻውን እንጦጦ ቁስቋም ማርያም መዳረሻውን ደግሞ እንጦጦ ፓርክ በማድረግ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ውድድር ተካሂዷል።

ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮች ቻሌንጆች ፤ ፌስቲቫል፣ የጫካ ሲኒማና ሌሎች ፕሮግራሞች ተካሂዷል።





Leave a Comment