banner

12 ሜኖታ ሰሚት ገባ

#FastMereja I 12 ሜኖታ ባርና ሬስቶራንት የአድራሻ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ። የ12 ሜኖታ ባለቤት ወ/ሮ የኔነሽ ገረመው ለፋስት መረጃ እንደገለፀችው ለአመታት ከሚታወቅበት ጋዜቦ አደባባይ አሁን የአዲስ አበባ አዲሷ ድምቀት በሆነችው ሰሚት ፍየል ቤት በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን ገልጻለች።

በአዲሱ አድራሻ ደረጃውን የጠበቀ ምቹ የቪአይፒ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ በሬስቶራንቱ የሀበሻ ምግቦች በተለይ ክትፎ በልዩ ሁኔታ እንደሚዘጋጅ እንዲሁም ለተለያዩ ዝግጅቶች የኬተሪንግ ስራ በስፋት እንደሚሰራ ወ/ሮ የኔነሽ ተናግራለች። 12 ሜኖታ በቀጣይ ትልቅ ሆቴል የመክፈት እቅድ ያላት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ለ25 ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል።

“12 ሜኖታ” ማለት 12 ሚካኤል ሲሆን “ሜኖታ” የጉራጊኛ ቃል ነው ትርጉሙም “ስራው” ማለት ነው አንድ ላይ “የሚካኤል ስራው” የሚል ትርጉም አለው።





Leave a Comment