banner

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በአድዋ ሙዚየም አካሄደ

#FastMereja I “ጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግስት ጠንካራ ሀገር” በሚል መሪ ቃል ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 26/2017 ዓ/ም በአድዋ ሙዚየም ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

በጉባኤው ላይ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ መለስ አለም ፣ የትግራይ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና ተወካዮች በሺ የሚቆጠር አባላቱና የየክልሉ የምርጫ አስተባባሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፓርቲው የትኩረት አቅጣጫውን ያደረገው ሰላምና ደህንነት ላይ፣ በቂ የምግብ አቅርቦት ላይ ፣ንጹህ የመጠጥ ውሀ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ላይ፣ ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት አገልግሎት ላይ ፣ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ላይ፣ የመኖሪያ ቤት አገልግሎት ላይ፣ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ፣ የስራ እድል መፍጠር ላይ፣ መልካም አስተዳደር እና የህግ የበላይነትን ማስፈን ላይ እና ድህነት ቅነሳ እና ኢኮኖሚ ልማት ላይ ማድረጉን በጉባኤው ላይ ተጠቅሷል።

የነእፓ ሊቀመንበር ዶክተር አብድልቃድር አደም ለፓርቲያችን 6ኛ አመት እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ካሉ በኋላ ፓርቲያችን ገና በጠዋቱ ጠንካራ ፓርቲ መሆኑን አስመስክሯል። ግባችን ጠንካራ ፓርቲ መገንባት እና በምርጫ አሸንፎ መንግስት የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግስት ጠንካራ ሀገር የማይነጣጠሉ እርስ በእርስ የተገናኙ ናቸው ብለዋል።





3 comments

Amanuel Dejene Gawiwa May 4, 2025 - 12:16 pm

ብልፅግና ፓርቲ ሁሉ አቃፊ ነው
ነው የሚንለው በምክንያት ነው 🥰 ድሮ ድሮ እንደዚህ በነፃነት አትሰበሰቡም ነበር።

Reply
Eyob Gera May 4, 2025 - 12:18 pm

ነፃነት መለሰ ቢመልስ ባይመልስ እኛ ምን አገባን
እኩል ባይሆን እኩል ቢሆን እኔ ምን አባቴ አገባኝ

Reply
Getnet Gashaw Dejenie May 4, 2025 - 12:18 pm

ok
ለእናት ፓርቲ ካውንተር ሆኖ የተመሰረተው የኃይማኖት ፓርቲ ይሄ ነው። ድሉ የእናንተ ነው።

Reply

Leave a Comment