0
#FastMereja I የአርቲስት ቀመር ዩሱፍ 50ኛ አመት የሙዚቃ ጉዞ እና የመጨረሻው የሙዚቃ አልበም እንዲሁም የሙዚቃ ኮንሰርት ሊካሄድ ነው።
ዛሬ ግንቦት 7/2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል አርቲስት ቀመር የሱፍ እና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
የመጨረሻው የሙዚቃው አልበሙ «ገላኖ» የሚሰኝ ሲሆን ሰኔ 15/2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል የአልበም ሪሊዝ ይካሄዳል፣ መስከረም 23/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ኮንሰርቱን የሚያቀርብ ሲሆን በቀጣይ በአዳማ፣ በሻሸመኔ፣ በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር በሀገር ውስጥ የኮንሰርት ጉዞ የሚያደርግ ሲሆን በባህር ማዶ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ አውስትራሊያ እና በአረብ ሀገራት ኮንሰርቱ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
አርቲስት ቀመር ዩሱፍ በ50 ዓመታት የሙዚቃ ጉዞ 7 የሙዚቃ አልበም፣ 50 ነጠላ ዜማዎች ለህዝብ ጆሮ አድርሷል። ቀመር ከኦሮምኛ ሙዚቃዎች በተጨማሪ ከ10 በላይ ቋንቋዎች የተጫወተ አርቲስት ሲሆን ሙዚቃዎቹንም ከ48 ሀገራት በላይ ተዟዙሮ አቅርቦዋል።
#ኪነ_ጥበብ





2 comments
ጨንቆን ነበር 🤭
ማነው ቀመር ኳስተጫዋች ነው