banner

ኢንጂነሩ ድምጻዊ ሙሉ የሙዚቃ አልበም ሰርቶ አጠናቀቀ

#FastMereja I ድምጻዊ እስራኤል በሻዳ “ናንዬ” የተሰኘ የሸጎዬ የአፋን ኦሮሞ ነጠላ ዜማው በበርካቶች የሚታወቀው ሲሆን አሁን “ቃሊ” የተሰኘ አዲስ የአፋን ኦሮሞ አልበም ሰርቶ ማጠናቀቁን ዛሬ በትውልድ ከተማው ቢሾፍቱ ፒራሚድ ሪዞርት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ቃሊ አልበም በርካታ አንጋፋና ወጣት የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሣተፉበት ሲሆን 12 ያህል ሙዚቃዎች ተካተውበታል።

አዲሱ ቃሊ አልበም ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በራሱ ዩቲዩብ ቻናል እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መንገዶች ለህዝብ እንደሚደርስ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።

ከአልበም ምርቃቱ በኋላም በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ እየተዘዋወረ የሙዚቃ ስራዎቹን እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

ድምጻዊ እስራኤል በሻዳ ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ኢንጂነር ተመርቆ በሞያው ለአመታት እየሰራበት ይገኛል።

#ኪነ_ጥበብ




1 comment

Gashaw May 24, 2025 - 12:53 pm

ዘፋኝ የሆነው የሚቀጥረው አጥቶ ነው 🧓

Reply

Leave a Comment