#FastMereja I በዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በዚህ አመት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ38 ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ33ኛ ጊዜ “በትምባሆ እና በኒኮቲን ምርቶች ላይ የትምባሆ ኢንዱስትሪ አሳሳችና ድብቅ ስልቶችን በማጋለጥ ወጣቶችን እንታደግ!” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከሌሎች ባለ ድርሻ ማህበራት ጋር በመሆን ቀኑን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው ዘመቻው የትምባሆ እና የኒኮቲን ኢንዱስትሪዎች ጎጂ ምርቶቻቸውን ማራኪ ለማስመሰል የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች በማጋለጥ ላይ እንዲያተኩር ተደርጎ ነው የተቀረፀው ተብሏል።
የቀኑ አከባበር ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የቁጥጥሩ ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች ሚዲያን በመጠቀም እየተሰሩ እንደሆነ ተገልጿል። የዚሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ አካል የሆነውና በየዓመቱ ግንቦት 23 የሚከበረው በዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን አንዱ ኩነት ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ቀኑን በተለያዩ ግንዛቢ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲከበር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሲሰራ መቆዩ ተብራርቷል።
እ.ኤ.አ በ2022 በአለም አቀፍ ደረጃ በበርካታ ሀገራት ከ38 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ13-15 ዓመት የሚሆኑ ወጣቶች የትምባሆ ምርቶችን እንደሚጠቀሙ የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል።
ትምባሆ በህግ ቁጥጥር የሚደረግበት ምርት ሲሆን በቅጠሉ ውስጥ ብቻ 7,000 በላይ ኬሚካሎችን በውስጡ ይዟል፡፡ ከእነዚህ ኬሚካሎች ውስጥ አብዛኞቹ ጎጂ ሲሆኑ በተለይ 70 የሚሆኑ ካንሰር አምጪ ኬሚካል ናቸው፡፡ ሲጋራ ማጨስ እና ሌሎች የትምባሆ ምርቶችን መጠቀም በሱስ ለመያዝ ለአደገኛ የሳንባ በሽታ ለካንሰር፣ ለልብ በሽታ መዳረግ፣ ለፅንስ መጎዳት በሚጨስበት አካባቢ በሚኖሩ እና በማያጨሱ ሰዎች ላይ.. ጭምር ከፍተኛ የሆነ የጤና መታወክ እና ሌሎችንም ጉዳቶች እያስከተለ ይገኛል፡፡





1 comment
የሚጨስበት መቼ ነው የሚከበረው?