banner

ቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ት/ቤት ያሰለጠናቸውን 105 ተማሪዎች አስመረቀ

#FastMereja I ቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ት/ቤት በ45ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 105 ተማሪዎች በቀነኒሳ ሆቴል አስመርቋል።

የተመረቁት ተማሪዎች በሜካፕ፣ በጥፍር፣ በጸጉር በአይላሽ ሽፋሽፍት የውበት ሞያ ዘርፎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ እንደሆነ ተነግሯል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ዝነኛ አርቲስቶች፣ የዲጂታል እና የመደበኛ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ በውበት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የድርጅት ባለቤቶችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝቷል።

የቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ት/ቤት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የውበት ትምህርት ለማድረስ ካለው ቁርጠኛነትና ትጋት ባለፈ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆነና ከፍለው መማር የማይችሉ ሴቶችን በመደገፍና በማበረታታት የሞያ ባለቤት በማድረግ ብሩህ ተስፋ ያላቸውና የፋይናንስ ነጻነት ያላቸው አምራች ዜጎች እንዲሆኑ እድሎችን በማመቻቸት ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ የትምህርት ቤቱ መስራች ሜካፕ አርቲስት ቃልኪዳን ፍርዱ ተናግራለች።

ቃል ኢንተርናሽናል ሜካፕ ት/ቤት ከተለያዩ የአውሮፓ ተቋማት ጋር የሀገራችን የውበት ኢንዱስትሪ ደረጃ ለማሳደግ እና ለተማሪዎቻችን የስራ እድሎችን ለማስፋት በስፋት እየሰራ ይገኛል።





1 comment

S Yedngle Lij Habtshi May 30, 2025 - 5:09 am

Kalkidan Firdu 😍
Jegnit 🙌🏾♥️

Reply

Leave a Comment