banner

ኢትዮ ሄልክስ በሀገራችን ተፈላጊ የሆነውን የጆሮ መርጃ መሳሪያ መስመጣት ጀመረ

#FastMereja I ኢትዮ ሄሌክስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር የጆሮ መስሚያ ማዕከል በሀገራችን ከሚገኙ ሂሪንግ ሴንትር (የመስሚያ ማዕከል) አንዱ ሲሆን የጆሮ የመስማት ችግርን ለመቀነስ እንዲሁም የሰውን የመስማት ያለበትን ደረጃ ለማሳወቅ የሚረዱ ጥንካሬ፣ ጥራት፤ ምቾት እና ቴክኖሎጂ የዘመኑ ዘመናዊ የጆሮ ማዳመጫ መርጃ ፤ የኦዲዮ ሜትሪ ልኬት መስሪያ መሳሪያዎች እና ለዚሁ ህክምና የሚረዱ አፕሊኬሽኖችን የያዘ የጆሮ ማዕከል ነው።

ተቋሙ ከቱርክ እና ከሌሎች ያደጉ ሀገራት በማስመረት የሚያመጣቸውን የጆሮ መርጃ እና የኦዲዮ ሜትሪ ልኬት መስሪያ መሳሪያዎች ወደ ስራ በማስገባት በጆሮ ማዳመጫ መሳሪያ እጥረት እየተከሰተ ያለውን ችግር ለማቃለለ እየሰራ መሆኑ ዛሬ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ ወደ ስራ መግባቱን የሚያሳይ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ ተነግሯል።

የመስማት ችግሮችን ሊያቃልሉ የሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የመስማት ብቃትን ለማሻሻል የሚረዱ ህክምናዎች ቢኖሩም ለአብዛኛው ሰው ተደራሽ አለመሆናቸውን በመድረኩ ላይ ተነግሯል።

የአለም የጤና ድርጅት በመላው አለም መስማት የተሳናቸው ሰዎች ቁጥር ከ1.6 ቢሊዮን ማለፉን ይገልጻል።





Leave a Comment