0
#FastMereja I “የእግዚዓብሔር ክብር የኪዳኑ ታቦት” የተሰኘ በፓስተር ዳንኤል መኮንን የተጻፈ አዲስ መጽሐፍ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚመረቅ ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
የመጽሐፉ ሽፋን ታቦት እና መስቀል የያዘ ሲሆን ታቦት እና መስቀል የእግዚዓብሔርን ክብር ከፍ የሚያደርጉ እንደሆነ ፓስተር ዳንኤል መኮንን በመግለጫው ላይ ተናግሯል።
መጽሐፉ አዲሱ ትውልድ በእግዚዓብሄር ላይ ያለው ክብር እንዲጨምር እና ከህይወት ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን እንደሚዳስስ ተገልጿል።
“የእግዚዓብሔር ክብር የኪዳኑ ታቦት” መጽሐፍ በ10 ምዕራፎች የተከፋፈለ እና በ310 ገጽ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
ፓስተር ዳንኤል መኮንን በአዲስ አበባ በጅማ እንዲሁም ከሀገር ውጪ በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በአውሮፓ አገልግሏል።
ከመጽሐፉ የሚገኘው ገቢ በአዋሬ ለሚገኘው ለወንጌል ብርሃን ቤተክርስቲያን ህንጻ ግንባታ ይውላል።





2 comments
❤️❤️
ጥምቀት እና ከተራ ሲደርስ እዩ ጣኦት ሲሉ እንዳልነበር አሁን ለቢዝነሳቼው ሲሆን የነገርናቼውን ይፆፉ እና ገበያውን ያጧጡፉታል ግሩም ነው ብቻ