banner

ቲክቶከሯ ጃኒ ተጨማሪ 7 ቀን በእስር ቤት ታሳልፋለች

#FastMereja I ቲክቶከሯ ጃኒ ገብሩ በአዲስ አበባ ከተማ ተይዛ ወደ ድሬደዋ ከተወሰደች በኋላ ከዚራ ፖሊስ ጣቢያ ትገኛለች።

ወጣቷ ለእስር ያበቃት በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ተናግራለች በተባለ ንግግር ሲሆን ዛሬ በድሬዳዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርባ ነበር።

ፖሊስ ከተከሳሿ ስልክ ጋር ያልሰራናቸው ምርመራዎች ስላሉኝ ተጨማሪ ቀናት ይሰጡኝ በማለቱ 7 ቀን በፍርድ ቤት ተፈቅዶለት ለሰኔ 9/2017 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ፋስት መረጃ ከኢትዮጲካሊንክ ሰምቷል።

ቲክቶከሯ ይፋዊ መጠሪያ ስሟ በሶሻል ሚዲያ እንደሚገለጸው “ስመኝ ገብሩ” ሳይሆን በፍርድ ቤት ወደ “ጃኒ ገብሩ” በመቀየሩ በዛሬው ችሎት በይፋዊ መጠሪያ በማድረግ ጃኒ ገብሩን ማስመዝገቧን ከኢትዮጲካሊንክ ዘገባ ተመልክተናል።

3 comments

ማህደር የሽወንድ June 9, 2025 - 3:07 pm

ያቺኛዋ ስትወጣ ይቺኛዋ መግባቷ ይበል የሚያሰኝ ነው👍

Reply
Bright Abiy Ahmed June 9, 2025 - 3:08 pm

የ Tiktok accountዎን ለ ዳንኤል ደመቀ ዉክልና አሰጡት

Reply
S Yedngle Lij Habtshi June 9, 2025 - 3:08 pm

Melat Nigussie ይሄው 😆

Reply

Leave a Comment