banner

ሞቢሊቲኢ ለ50 ደንበኞች መኪና አስረከበ

#FastMereja I ሞቢሊቲኢ ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር ለ5ኛ ጊዜ የመኪና ርክክብ ዛሬ ሰኔ 7/2017 ዓ.ም አድርጓል

በዛሬው እለት ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ቆጥበው ሲጠባበቁ የነበሩ ለብድር ብቁ የሆኑ 50 ደንበኞችን የአምስተኛ ዙር የቢዋዲ መኪኖችን ርክክብ አድርጓል።

ሞቢሊቲኢ ከቢዋይዲ ሲጉል፣ ቢዋይዲ ኢ2፣ ቢዋይዲ ዩአን አፕ፣ ቢዋይዲ ዩአን ፕላስ እና ቢዋይዲ ሶንግ ፕላስ መኪኖችን በ50% ቅድመ ከፍያ ብቻ ቀሪውን ከድጋፍ ማይከሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር በ16.5% ወለድ ለደንበኞች እያቀረበ ይገኛል።

በዚህም መሰረት ከሞቢሊቲኢ ጋር የመኪና ግዢ ፈጽመው ሲጠባበቁ ከነበሩት ውስጥ ለ50 ደንበኞች የቁልፍ ማስረከብ ስነስረአት በዛሬው እለት አከናውኗል።

ሞቢሊቲኢ በ4 ዙር ያስረከባቸው ደንበኞች ለፈለጉት የተለያየ አላማ በቃሉ መሰረት ስለደረሰላቸው ልዩ ምስጋና አቅርበዋል እንዲሁም በቀጣይም የተለያዩ የኤሌትሪክ መኪናዎችን ከድጋፍ ማይከሮ ፋይናንስ ጋር ለማቅረብ ዝግጅቱን የጨረሰ ሲሆን፤ እስካሁን ከድርጅቱ ጋር አብረው የሰሩትን አካላት ምስጋና አስተላልፈዋል።

ሞቢሊቲኢ በ4 አመት የብድር ክፍያ መመለሻ ጊዜ ያቀረበውን የአጭር ጊዜ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ሪፌንቲ በሚገኘው ዋናው ሾውሩም እንዲሁም መስቀል ፍላወር እና ሃዋሳ ፒያሳ ሩት ገበያ በሚገኙት ቅርንጫፎች አመቻችቶ ተጨማሪ ዙር መኪኖችን ለማስረከብ ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡





1 comment

Fkru Gebre Meskel June 14, 2025 - 10:01 am

16.5% 😁😁

Reply

Leave a Comment