#FastMereja I የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) ከፍተኛ የጤናው ዘርፍና የተቋሙ አመራሮች በተገኙበት የአህሪ የ55 ዓመታት የምርምር፣ የፈጠራ፣ ልማት እና ምርት ሥራዎች ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሂዷል።
አህሪ ባለፉት 55 ዓመታት በጤናው ዘርፍ የምርምር ልማትን ለማሳደግ በርካታ የምርምር ውጤቶችን በማውጣት ለሀገራችን ብሎም ለዓለም አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ የሚገኝ ተቋም መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ እንደገለጹት “ባለፉት ዓመታት በምርምር ተቋሙ የወጡ ውጤቶች እንደ ሀገር ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ የህክምና ስርዓቶች እንዲቀየሩ አድርገዋል።” ብሏል።
የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በጤናው ዘርፍ የሚደረጉ የምርምር እና ልማት ስራዎች ስኬታማ ሆነው ማህበረሰቡ ጋር የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጡ ሁላችንም የሚመለከተን ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብሏል።
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ባዮሜዲካል፣ ክሊኒካል፣ የክትባት፣ ዲያግኖስቲክስና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ምርምርና ልማት፣ የባህላዊና ዘመናዊ መድኃኒት ምርምርና ልማት እንዲሁም የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።




