#FastMereja I የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በቅርቡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የፓርኪንግ ክፍያ ሲስተም (Parking Management System) በሁሉም የተሸከርካሪ ማቆሚያ ቦታዎች ላይ ተግባራዊ አድርጓል፡፡
የፓርኪንግ አይነቶች
• የመንገድ ዳር (On street parking
• የህንፃስር ( Basement parking )
• የተከለለ ( Surface parking )
• የህንጻ ላይ የተሸከርካሪ ማቆሚያ ( Parking Building) System)
ለአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በሙሉ!
• ክፍያው ለጊዜው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ፓርኪንግ ብቻ ነው፤
• ወደፊት በሌሎች ክፍያ አማራጮች ይከናወናል፣
• በሲስተም ስራ በጀመሩ ማህበራት ላይ ጥሬ ብር (ካሽ) መክፈል አይቻልም፣
• ወደ ተሸከርካሪ ማቆሚያው ሲገቡ የያዙትን ተሸከርካሪ ሰሌዳ ቁጥር፣ መልክት (መረጃ) እንዲደርስዎ የያዙትን ስልክ ቁጥር ለሲስተሙ ባለሙያ ያስመዝግቡ፣ (For Check-in)
• ከተሸከርካሪ ማቆሚያው ሲወጡ የመውጫ መልዕክት መድረሱን ያረጋግጡ (For Check out). (መልዕክት የሚይዘው የቆዩበትን ሰዓት፣ የክፍያ መጠን፣ የመክፈያ ኮድ PT….) PT…. ባለ ሶስት ወይም ባለ አራት ወይም ……..ዲጂት ቁጥር የመክፈያ ኮድ ነው፡፡
• ክፍያውን በ24 ሰዓት ውስጥ ካለምንም ወለድ በተጠቀሱት የክፍያ አማራጮች መክፈል ይቻላል፣ ከ24 ሰዓት ካለፈ ወለዱ እየጨመረ ይቀጥላል፣
• ያለብዎትን እዳ ካልከፈሉ ከአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ዙሪያ የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት አይችሉም
• የሞብይል አፑን ከፐሌይ ስቶር በማውረድ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ
• የክፍያ መጠን በሰዓት መነሻ በ30 ደቂቃ ብር 20 /ሃያ/ ነው
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

7 comments
አላነሰም ?
Impossible to have car in addis lol
Yasafral
ተሸክመውት ነው እንዴ ሚቆሙት ልባ ቸው ይቁምና 😭😭😭
በቅርቡ ለምንተነፍሰው አየርም ያስከፍለናል
What is going on
Pp መንግስት
#ሆላ_ማጋኖ🙏