banner

ኢትዮጲያ የጋዝ ምርትን ወደ ገበያ ልታቀርብ ነው፡፡

#FastMereja I ኢትዮጲያ የራሷን ጋዝ ለማምረት ጥረት ስታደርግ መቆየቷ የተገለፀ ሲሆን በመጪው መስከረም የ 2018 ዓ/ም አዲስ አመት ላይ ወደ ገበያ ሊቀርብ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ይህ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በሀገሪቱ ከሚገኙ የሚዲያ አመራሮች እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር በዛሬው ዕለት እያደረጉት ባለው የጋራ ውይይት ላይ ነው፡፡

በዚህ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጲያ ማዳበሪያን ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ለማምረት ከስምምነት ላይ መድረሷንም አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ውጥን መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመንግስትን የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ወቅት መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

በወቅቱም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው ከ2.5 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረው ነበር፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪው የ 2018 መስከረም ወር ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ሪቫኑ እንደሚቆረጥ በዚሁ መድረክ ላይ አንስተዋል፡፡

ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው

10 comments

መንግስቱ እራስ አርበኛ ዘመነ June 23, 2025 - 12:02 pm

ጋዝ ሀሀሀሀሀሀሀ የጋዛ ሰርፅ ሊዘጋ ነው😂😂😂

Reply
Lijalem Melie June 23, 2025 - 12:02 pm

ሰክሶ አደር የሆነ ሰው😂

Reply
Mohammed Hasen June 23, 2025 - 12:02 pm

በለው ውሸት😂

Reply
Abe Mamo June 23, 2025 - 12:02 pm

አቤት ሳክስ 😘😘😘

Reply
Bęñźęmã Mãŋ June 23, 2025 - 12:03 pm

በምላሱ ነው?🤔

Reply
ሰው በሰው አዘነ ከየጋግና June 23, 2025 - 12:03 pm

አውርቶ አደር

Reply
Teda B Man June 23, 2025 - 12:03 pm

በወሬ እኮ እስካሁን ከቻይና ቀጥለን ከዓለም 4ተኛ ሁነን ነበር😋😏

Reply
በዘላለም መውደድ ወዶኛል June 23, 2025 - 12:04 pm

ኢራን ጉድ ሆነች በሉኛ 😂😂😂

Reply
Mulu Tesfa June 23, 2025 - 12:04 pm

አይመቸህ

Reply
Natinael Samuel June 23, 2025 - 12:04 pm

የሃበሻ ተርት ስገጥም ጋዝ ጋዝ የምል ዜና ይሉታል ይሄ ነው

Reply

Leave a Comment