banner

ዓለም አቀፍ የፈርኒቸር ውጤት አምራች የሆነው አሽሊ ፈርኒቸር የኢትዮጵያን ገበያ ተቀላቀለ

#FastMereja I ዋና መሥሪያ ቤቱ በዊስኮንሲን ዩኤስኤ የሚገኘው አሽሊ ፈርኒቸር ኢንዱስትሪዎች በዓለም ላይ ትልቁ የቤት ዕቃዎች አምራች ነው። በ155 ሀገራት ከ30ሺ በላይ ሰራተኞች ያሉት አሽሊ ፈርኒቸር ዛሬ ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም ምርቶቹን በኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ በኢትዮጵያ ቅንጡ ፈርኒቸሮችን በማምረት ከሚታወቀው ዩስራ ሆም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

በዚህ ልዩ አጋርነት ስምምነት መሰረት ዩስራ ሆም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የአሽሊ ፈርኒቸር ውጤቶችን በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በማስገባት እንደሚሸጥ የዩስራ ሆም መስራች እና ስራ አስኪያጅ ዩስራ ኑርሁሴን ለፋስት መረጃ ገልጿል።

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የአሜሪካው አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝቷል።

ዩስራ ሆም ከተመሰረተ አምስት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ለመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ለግል ተቋማት ቅንጡ ፈርኒቸር ውጤት ሲያቀርብ ቆይቷል።





Leave a Comment