#FastMereja I በግሪንዌቭ አሊያንስ አስተባባሪነት ለተከታታይ ስድስት አመታት ሲካሄድ የቆየው የአርቲስቶች፣ የአትሌቶች፣ የጋዜጠኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ዘንድሮ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ጀልሚ ኢንሲሳሌ ቀበሌ የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማሃዲ፣ የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ፣ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም አርቲስቶችና የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም መርሃ ግብር ተካሂዷል።
የግሪንዌቭ አሊያንስ መስራች አቶ ሚኪያስ ነጋሳ ባስተላለፈው መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ሳይቋረጥ በተከታታይ እንዲካሄድ ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረበ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች የኢትዮጵያ አከባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ላለፉት 6 አመታት የአረንጓዴ አሻራ መረሃግብር መሳካት ከፍተኛ አስተዋጾ ላደረጉ ተቋማት፣ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች እውቅና ተሰጥቷል።
ይህንን ፕሮግራም በፕላቲኒየም ደረጃ ላለፉት 6 አመታት ስፖንሰር ያደረገው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮሮፕሬሽን ሲሆን ዘንድሮ ግሪንዌቭ አሊያንስ ከኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስተር፣ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁም የምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳደር በጋራ አዘጋጅተውታል።





3 comments
አሻራ ለሀገራችን ብልፅግና
መንሱር ጋዜጠኛ ኖ?😁
እና መንሱር ምን ይሠራል።