banner

“የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ” ተመረቀ

#FastMereja I የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ “ከመሀቡብ ቴክኖሎጂስ” ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐርአፕ” በሚል መጠሪያ መልከ ብዙ ገፅታንና ይዘትን የተላበሰ እያዝናና የሚያስተምር የሞባይል መተግበሪያ ሰርቶ በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት በድምቀት በስካይ ላይት ሆቴል አስመርቋል።

የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ፤ በሀገራችን የሙሉ ጊዜ የልጆች የቴሌቪዥን ቻናል በመጀመር ፈርቀዳጅ የሆነና በተለይም በልጆችና ቤተሠቦቻቸው ዘንድ ሠፊ ተቀባይነት በማግኘት በአወንታዊ የትውልድ ግንባታ ላይ ሳያሰልስ እየሠራ የሚገኝ ተቋም ሲሆን ተማሪ ቤት፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ ሥነ-ምግባር፣ ጠፋጭ ታሪኮችን ጨምሮ ከ1ዐ ዓይነት በላይ ይዘቶችን በአንድ አፕ ላይ መጠቀም የሚያስችል በተለይም ለተማሪዎች እያዝናና በማሳወቅ ረገድ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል፡፡

“የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ” በዲጂታል አማራጭ የልጆችን ነገ ብሩህና ቀና በማድረግ ረገድ፤ የወላጆችን ድካም የሚያቀል በአንድ ማዕድ ሠፊ ገበታን የያዘ እንደሆነ ተነግሯል።





Leave a Comment