banner

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር የተመሰረተብበትን 10ኛ ዓመት ሊያክብር ነው

#FastMereja I የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት ለሦስት ወራት የሚቆዩ የተለያዩ ሁነቶችን አቅዶ እየሰራ እንደሆነ ዛሬ ሀምሌ 18 ቀን 2017 ዓ/ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

ማህበሩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገርበሚኖሩ ውድድሮች በተለይም በሁለቱም ፆታዎች በወንዶችና በሴቶች ብሔራዊ ቡድኖችን በመደገፍ የራሱን የማይተካ ሚና እየተወጣ እንደሆነ ተገልፆል፡፡ ከዚያም አልፎ በሃገራችን በተለያዬ ጊዜ በሚፈጠሩ የተፈጥሮና ሰው ስራሽ አደጋዎችና ችግሮች ህብረተሰቡን በተለይ አዲሱን ተተኪ ወጣቱን ትውልድ በማስተባበር በሃገራዊ ፍቅርና ስሜት በማነሳሳት በተሟላ እምነትና ፍላጎት በመሳተፍ ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ ነው ተብሏል።

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የደጋፊ ማህበሩ በኩላሊት ህመም እየተሰቃዩ ለሚገኙ የድሮ የብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሀይለስላሴ ገ/ጊዮርጊስ (ሀይላት) እንዲሁም ለቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ይልማ ከበደ (ጃሬ) ለእያንዳዳቸው የሃምሳ ሺህ ብር ድጋፍ አርጓል።

ማህበሩ ከዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ በማስቀጠል የሚያካሂደውና በአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት ንቅናቄ ለማስጀመር ዓላማ ያደረገው አዲስ ዎክ ኤንድ ፒክና የጎዳና ላይ ትርኢትን ጨምሮ የባለሙያዎች የስፖርት ውድድር፣ የአዲስ ማስ ሰፖርት፣ ዲፕሎማቲክ ስፖርት ፌስቲቫል ስፖርት ለሰላም ሀገር አቀፍ የስፖርት ውድድር ፣ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌስቲቫል፣ እንዲሁም ስፖርት ላይ ለሰሩ ባለሙያዎችና ተቋማት እውቅና የሚሰጥበት መርሃግብር ከአከባበሩ ሁነቶች መካክል መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ማህበሩ ከቴምር ፕሮፐርቲስ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።





1 comment

Cr Biruk July 25, 2025 - 7:04 pm

እንጀራው ሳይኖር ወጡ ተሰራ አለች አያቴ ብሔራዊ ቡድኑ ሳይኖር ደጋፊ ማህበርም አለን

Reply

Leave a Comment