0
#FastMereja I ሰክሰስ ፕላስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ማህበር 4ኛ ዙር ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጕዳይ ቢሮ እና ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጕዳይ ቢሮ ጋር በመሆን 1ሺህ ዊልቼር የመስጠት እቅድ ውስጥ ዛሬ ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም በኢሊሊ ሆቴል ለ100 አካል ጉዳተኞች ዊልቸር አበርክቷል።
የዊልቸር ድጋፉ በቀጣይም በተከታታይ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን ሰክሰስ ፕላስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ማህበር ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል ጋር በቀጣይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ፈጽሟል።




