0
#FastMereja I ባወዚር ትሬዲንግ ዛሬ ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም በሸገር ከተማ አስተዳደር በሸገር ማረሚያ ቤት የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ቤቶች ዋና የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት “የስራ እድል ፈጠራ” በሚል ርዕስ የመክፈቻ እና የስራ ማስጀመርያ ስነስረዓት ተካሄዷል።
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን እና የባወዚር ትሬዲንግ ንግድ ድርጅት መካከል በተደረገ ስምምነት በሸገር ከተማ ማረሚያ ቤት ለታራሚዎች የኢንዱስትሪ ልብስ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት፣ ገጠማ/ተከላ እና ጥገና እንዲሁም ነጻ ስልጠና በመስጠት የሙከራ ፕሮጀክት መተግበሪያ ስምምነት ተፈጽሟል።
የባውዚር ትሬዲንግ ባለቤት አቶ መሐመድ ሰዒድ ባደረጉት ንግግር ለታራሚዎች የጋርመንት ሥልጠና በመስጠት በማረሚያ ቤቱ ቆይታቸው ሞያ ይዘው በመውጣት ወደ ማህበረሰቡ ሲመለሱ የሰው እጅ ጠባቂ ሳይሆኑ አምራች ዜጋ በመሆን ራሳቸውን ቤተሰቦቻቸውን ከማስተዳደር አልፈው በአገር ግንባታ ውስጥም የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል እንደሆነ ገልጸዋል።
ባወዚር ትሬዲንግ ንግድ ድርጅት በ2010 ዓም የተመሰረተ ሲሆን ኤሌክትሮኒክስ እና ማሽኖችን ኢምፖርት ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው።




