banner

ስፖርቱ ለዋንጫ ሳይሆን ህይወትን የሚለውጥ ነው

#FastMereja I አገራችንን በመወከል ከ13 የዓለም አገራት ከተውጣጡ ግራንድ ማስተሮች ሲሰጥ የነበረው የጂቲቲኤፍ ስልጠና ውድድር በነገው እለት እንደሚጠናቀቅ ታወቀ።

ዶክተር ሙን ከኮሪያ ፣ የዓለም ቴኳንዶ መስራች የሆኑት ግራንድ ማስተር ጁሊ ፣ ከአገራችን ዶ/ር ግራንድ ማስተር ሔኖክ ግርማ እንዲሁም ግራንድ ማስተር ሲን የተሳተፉበት ይህ ስልጠና ከኢትዮጵያ ከሁሉም ክልልሎች እንዲሁም ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ የተውጣጡ ሰልጣኞችን አሰልጥኗል።

የስልጠናው ዋና ይዘት ትውልዱ በአካል በአእምሮ በስነ ምግባር በመንፈስ ጠንካራ እና አምራች ዜጋ እዲሆን የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር የፍልሚያ አሸናፊ ሳይሆን በህይወት ፈተና በብቃት ማሸነፍ የሚያስችል መሆኑ ተነግሮለታል።

በዚህ ውድድር አሸናፊ ለሆኑት የወርቅ፣ የብር፣ የነሀስ ሜዳሊያ እንዲሁም ከሁሉም አሸናፊው የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል ተብሎ ይታሰባል።





Leave a Comment