0
#FastMereja I የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደብረማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ተገጣጣሚ ድልድይ በፍጥነት በመንገንባት ለአገልግሎት ለማብቃት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ድልድዩ በጎርፍ የተወሰደዉ ነሐሴ 3/2017 ሌሊት ጮቄ አካባቢ በጣለዉ ከባድ በተፈጠረ ጎርፍ ነዉ። ድልድዩ ጥዋት አካባቢ እንደተወሰደ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደብረማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ስለጉዳዩ ጠይቀናቸዉ ችግሩ መከሰቱን ገልጸዉ ተገጣጣሚ ድልድይ ለመስራት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በዛሬዉ እለት ከአዲስ አበባ መጫን መጀመራቸዉን ገልጸዉልናል።
የጌደብ ወንዝ በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር የዉላ ቀበሌ አካባቢ የሚገኝ ወንዝ ነዉ።
በተመሳሳይ በዚሁ ወንዝ ላይ የአንጎት በለምና ቀበሌ ነዋሪዎችን ከአማኑኤል ከተማ ጋር የሚያገናኝ የብረት ድልድይ በጎርፍ ተወስዷል።
ፎቶ የማቻከል ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነዉ።

3 comments
ከጦርነቱ ይልቅ ድልድዩን ስሩት ህዝብ አይሰቃይ
በማስቲክ የምታጣብቁትን ነገር አተውም ወይ 😎
Fano ወስዶት እንዳይሆን?