banner

በአዲስ አበባ ቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች እየታሸጉ መሆኑ ተነገረ

#FastMereja | በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታሸጉ መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በወጣቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ እነዚህ ቤቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ፣ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

ይህ መታሸግ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋለ ቢሆንም፣ በተለይም በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የሚገኙ በርካታ የቢንጎ ቤቶች በዛሬው ዕለት መታሸጋቸው ካፒታል ተመልክቷል።

አንዳንድ የጨዋታ ቤቶቹ ባለቤቶች እንደተናገሩት፣ መታሸጉ የተፈጸመው “አዋኪ ድርጊት” ፈጽመዋል በሚል ምክንያት ነው። በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እነዚህ አጫዋቾች፣ እርምጃው ቀጣይነት እንደሚኖረው እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

ምንም እንኳ እነዚህ ቤቶች ዋነኛ ተግባራቸው የቢንጎ ጨዋታ ማቅረብ ቢሆንም፣ ከጨዋታው በተጨማሪ የጫት መጠቀሚያ እና ለህገወጥ ወንጀሎች መነሻ ቦታዎች እንደሆኑ እና ይህንንም መንግስት ለማስቆም በሚል እርምጃውን እየወሰደ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

በተለይ በአዲስ አበባ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በስፖርት ውድድር ላይ የሚደረጉ የውርርድ (ቤቲንግ) ጨዋታዎችን ከማሸግ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንዲገኝ የሚታወቅ ሲሆን አሁን የቢንጎ ቤቶች መታሸግ ከዚህ ጋር ግንኙነት ያለው ስለመሆኑ ግን እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ ነገር የለም።

ዘገባው የካፒታል ነው

10 comments

Biniyam Wegena Jr. August 18, 2025 - 6:47 pm

እሰይ

Reply
Biniyam Wegena Jr. August 18, 2025 - 6:47 pm

ጆዬ ጃንታ Challenge

Reply
Alex Mamo August 18, 2025 - 6:48 pm

ገንዘቤ ካለቀ በኋላ ምን ጥቅም😭😭😭😭

Reply
BecKi Mas August 18, 2025 - 6:49 pm

mesrat yalbachew wesen balgizewoch mhon selalbet awe

Reply
Liked Alem Alemayehu August 18, 2025 - 6:50 pm

Closed

Reply
Diriham Jaarsee Abush August 18, 2025 - 6:50 pm

Tiru nw bezaw online qomaroch bizegu bay negn menor alchamem

Reply
Dinkayahu Adugna Abreham August 18, 2025 - 6:50 pm

ቤቲንግ የሚባል ነገር ቢከለከል እኛ ወጣቶች ስራ ፈጣሪ እንሆን ነበር😭😭😭

Reply
Wondimu Dinka August 18, 2025 - 6:51 pm

Nifas silk lafto w.11 endale bezaga bay neng

Reply
Leta Bekele August 18, 2025 - 6:51 pm

They have to replace by beting

Reply
Achro Be August 18, 2025 - 6:52 pm

አይዘጋም ኦዱ ስንት ነው

Reply

Leave a Comment