#FastMereja I ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡
📌 ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ 6 ሺህ ብር
📌 ፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ 39 ሺህ ብር
📌የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ 11 ሺህ 500 ብር
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡
በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡
በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ነው ያለው።
ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21 ሺህ 492 ወደ ብር 39 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።
የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 የሚሻሻል መሆኑን ገልጿል።
ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አስታውቋል።
ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል ያለው ኮሚሽኑ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ብሏል።
ዘገባው የፋና ነው

10 comments
ምርጫ ደረሰ
ግድ ነው በልቶ ማደር ይቅደም ከመብለጭለጭ
መንግሥት እንደሀገር የመንግሥት ሠራተኛውን ኑሮ ለማሻሻል ጥረት እያደረገ ብሆንም ከሥር በክልል ፣በዞንና በወረዳ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ከላይ በሚወርደው ልክ ለሠራተኛው ቅድሚያ እየሰጡ ያለመሆናቸው ግልጽ ስሆን:-
በሌላ በኩል ደግሞ የደመወዝ ማሻሻያውን ተከትሎ የሚመጡ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎች ጭምር ለመቆጣጠር መንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥተው ካልሰራ የነገ የኑሮ ማሻሻያ የተባለውን ቃላቶችን አፈራሽ እየተደረገ መሄዱ አይቀረ ጉዳይ ነው ::
ይህ ሆኖ ባለበት የደሞወዝ ማሻሻያ ተደረገ ማለት አሁንም የኑሮ ቀውስ በከፍተኛ ሁነታ እንደምያስከትል ማንም ልገነዝበው የምገባ ጉዳይ መሆኑን ለማሳሰብ እንደ ግል አሰታየት‼
ቢሆንም በመጨረሻ በዚህ ጉዳይ መንግስት የደሞወዝ ጭማረ መገለጫ ከመጨመሩ አሰቀድመወዝ ማውጣት የምያስከትሉ የዋጋ ጭማረወች ላይ በተደጋጋም ልዩ ትኩረት በመሰጠት መሰራት እንደለበት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አሰታየት በመሰጠት ሚና መጫወት አለባቸው‼‼✔
Zeyit ayigezam
ጻ 😂
Account ላይ ሳይገባ አላምንም
ጥሩ ዜና ነው🙏 እንድህ ከሆነማ የንግዱ ማህበረሰብ ዜናውን እንደሰሙ ምን እንደሚያደርጉ ቀድመው ስለሚያስቡ የሰራተኞች ጠላት እነርሱ ናቸውና ጥብቅ ክትትል መደረግ አለበት።
አላምንም ወሬ ነው
ኡፍፍፍፍ አሁን ደግሞ ስለኑሮ ላስብ? ተጨማሪ ኑሮ ውድነት
ይህን ዜና አብዱ ባለሱቁ እና ቲመርጋ ባለ ግሮሰሪዉ ከሰማ ጉድ ነዉ😁😁😁