#FastMereja I ቻናል ዋን የተሰኘ አዲስ የመዝናኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ወደ ስርጭት ሊገባ እንደሆነ ዛሬ ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ አዲስ የቤተሰብ መዝናኛ ጣቢያ ነው የተባለው ሚዲያው ዋናው ራዕይም ጥራት ባላቸው በልዩነት በሚቀርቡ ተመራጭ ፕሮግራሞች መላው ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦችን በአንድ ላይ ማሰባሰብ እንደሆነ ተገልጿል።
ቻናል ዋንን ለማቋቋም ስናልም ራሳችንን የጠየቅነው የመጀመሪያው ጥያቄ ልክ እንደ ቤተሰባችን ቅርብ የሆነ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሊወደው የሚችል በአሁኑ ሰዓትም የኢትዮጵያን እውነተኛ መንፈስ የሚያንፀባርቅ ቤተሰባዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቢኖር የሚል ነበር ያሉት የጣቢያው መስራች የሆኑት አቶ ሳሙኤል ደበበ ናቸው።
የቴሌቪዥን ጣቢያችንን ስንጀምር ከቴክኖሎጂና ኢንቨስትመንቱ በላይ ዋንኛ የትኩረት ማዕከል ያደረግነው ሰዎችን ነው ስለሆነም የሰዎችን ፍላጎት ማርካትን መሰረት አድርገን፣ በምርጥ የታሪክ አቀራረብ፣ ቤተሰብን ብሎም ማህበረሰብን ማቀራረብ እና አብሮ በጋራ መዝለቅም ዋነኛ ተግባራችን ነው ብሏል።
ከ80 መቶ በላይ አዳዲስ (ኦርጂናል) ይዘት ያላቸው ኢትዮጵያዊ ድራማዎች፣ ኮሜዲዎች! ሪያሊቲ ሾዎች፣ ጌም ሾዎች፤ ስፖርታዊ ፕሮግራሞች፤ ሙዚቃዎች ትምህርታዊ ፕሮግራሞች የልጆች ዝግጅቶች ለትውልድ በሚመጥን መልኩ የተዘጋጁ እንደሆነ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።
በኢቢኤስ ጣቢያ እና በሌሎች ሚዲያዎች ላይ የሰሩ ፕሮግራም አቅራቢዎችን ይዞ መምጣቱ ተገልጿል።
ቻናል ዋን ላለፉት 2 ወራት የሙከራ ስርጭት ላይ የቆየ ሲሆን እሁድ ነሐሴ 18/2017 ዓም መደበኛ ስርጭት እንደሚጀምር ተገልጿል።





2 comments
ለቻናሉ frequency የለውም እንዴ?
ኢትዩ ሳት ላይ አለ እንዴ ቻናሉ?