0
#FastMereja I እንጆሪ፤ እንጃ፣ እወድሻለሁ፣ እቱ በተሰኙ ነጠላ ዜማዎች የሚታወቀው ድምጻዊ አዲስ ለገሰ “ማስታወሻ” የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሰርቶ እንዳጠናቀቀ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
“ማስታወሻ” 14 ዘፈኖችን ያካተተ አልበም ሲሆን በዜማና በግጥም ይልማ ገ/ብረዓብ፥ ሞገስ ተካ፣ አብነት አጎናፍር፥ ቢንአሚር አህመድ ፥ ዓለማየሁ ደመቀ፥ አንተነሀ ወራሽ፥ እሱባለው ይታየው፥ ናትናኤል ግርማቸው ፥ አስታወሰኝ ረጋሳ፥ እዮብ ዕድሉ፥ ዳዊት ተስፋዬ እና ራሱ አዲስ ለገሰም ተሳትፈውበታል።
በሙዚቃ ቅንብሩ ሚካኤል ሃይሉ፣ ኪሩቤል ተስፋዬ፣ ብሩክአፈወርቅ፥ ኤንዲ ቤተ ዜማ፥ እና ኤርሚያስ ሞላ ተሳትፈዋል፡፡ የማስተሪንግ ስራው በኪሩቤል ተስፋዬ ተከናውኗል።
“ማስታወሻ” አልበም ስራን ጀምሮ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመታትን የወሰደ ሲሆን አልበሙ በርካታ የሙዚቃ ዘይቤዎችን እና ዘውጎችን ያካተተ እንደሆነ ተነግሯል።
አልበሙ ቅዳሜ ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ለገሰ ይፋዊ ዩትዩብ ቻናልና በሁሉም ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች ይደርሳል።
#ኪነ_ጥበብ





2 comments
3አመት የፈጀበትን በ3ቀን እንዳይሰለቸን ጥንቃቄ ያሻል””
ሙዝቃ መስራትም ሦስት ዓመት ይፈጃል ከንቱ ዓለም