banner

“ዘመን ገበያ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ኤክስፖ 2018″ የአዲስ ዓመት ባዛር ተዘጋጀ።

#FastMereja I ታሜሶል ኮሚዩኒኬሸን “ዘመን ገበያ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ኤክስፖ 2018″ የተሰኘ የአደሰ ዓመት ኤግዚቢሸን አና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሸን ማዕከል ከነሐሴ 17 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ አንደሚያካሄድ ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም የታይትል ስፖንሰርነት እና ኤክስክሉሲቭ የክፍያ አጋርነትን በመጠቀም እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከቴሌብር ሱፐርአፕ ጋር ተዋህዶ የተዋወቀውን የ“ዘመን ገበያ” የዲጂታል ግብይት መተግበሪያን በስፋት ለማስተዋወቅና በማሰብ ኤክስፖው “ዘመን ገበያ አዲስ ነገር በአዲስ አመት ኤክስፓ 2018″ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

በዚህ ኤክስፖ 19 ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ከህንድ፣ ከቱርክ፣ ከቻይና፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ከሌሎች ሀገራት የመጡ ኤግዚቢተሮች በመኖራቸው፣ ግብይቱ አለም አቀፍ ያደርገዋል ተብሏል። በዚህ ዓመት ከ300 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ምርቶችን ይዘው ይቀርባሉ።

ከትምህርት ቁሳቁስ እና የቤት ዕቃዎች እስከ ቴክኖሎጂ እና አላቂ አቃዎች ድረስ ሰፊ ምርጫ መኖሩ ተገልጿል።

በኤክስፖ ግቢ ውስጥ፣ ፋይናንስ መንደር የሚል ልዩ ቦታ የተዘጋጀ ሲሆን ዋና ዋና ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማትን ያስተናግዳል።

የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ቅዳሜ ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይከፈታል።





Leave a Comment