0
#FastMereja I አዲስቪዥን ትሬዲንግ ኃ/የተ/ግ/ማ በኢትዮጵያ ትልቁ እና ሁሉን አቀፍ ትምህርታዊ ዝግጅት አዲስ ቪዥን የትምህርት ኤክስፖ 2025 ማዘጋጀቱን ገለጸ።
ኤክስፖ ትምህርት ቤቶችን እና ተማሪዎችን በሚያገለግሉ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የትምሀርት ተቋማትን፣ አቅራቢዎችን፣ አምራቾችን እና አገልግሎት ሰጪዎችን አንድ ላይ በአንድ ቦታ በአንድ መድረክ እንደሚያገናኝ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል።
ተሳታፊዎች ከብዙ ባለድርሻ አካላት ጋር ለመገናኘት፣ አዳዲስ ምርቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ለመተዋወቅ እንዲሁም አዳዲስ ትምህርታዊ መፍትሄዎችን በአንድ ማእከላዊ ቦታ የማግኘት እድል ይኖራቸዋል ተብሏል።
በዚህ የትምህርት ኤክስፖ የትምሀርት ተቋማት፣ የትምህርት ቁሳቁሶችን፣ ዩኒፎርሞችን፣ አልባሳትን፣ መጫወቻዎችን እና የመጫወቻ ሜዳ አቅራቢዎች ምርታቸዉን እና አገልግሎታቸዉን ያስተዋውቃሉ።
በሥርዓተ ትምህርት ልማት፣ በትምህርት ፈጠራ እና በሙያ መመሪያ ላይ የፓነል ውይይቶች ይደረጋል እንዲሁም ተማሪዎች፣ ለወላጆች እና ለአስተማሪዎች የሚያወያዩበት መድረኮች ይካሄዳሉ።
ኤክስፖ ከነሀሴ 22-24/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በግዮን ሆቴል ይካሄዳል።




