0
#FastMereja I ድምፃዊት ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ አዲሱን አልበሟን ማጠናቀቋን ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግራለች። “ደህና ሰው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አልበም አስፈላጊው ስራው ተጠናቆ ለመቅረብ ዝግጁ ሆኗል::
ድምፃዊቷ ስራዋን ለማስተዋወቅ እና በይፋ ለህዝብ ለማድረስ ማክሰኞ ነሀሴ 20/2017ዓ.ም ቀጠሮ ይዛለች::
ስለ አልበሙ ዝርዝር መረጃ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግም ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ከድምፃዊቷ ሰምቷል::
ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ በ2008 ዓ/ም ለመጨረሻ ጊዜ ለህዝብ ያደረሰችው “ምስክር” የተሰኘ አልበሟን እንደሆነ ይታወሳል።
#ኪነ_ጥበብ

2 comments
አላገባችም እንዴ አምሮባታል ❤
ደህና ሰው አግኝታ ይሆን🙏