0
#FastMereja I ገንቢዎችን ለማበረታታት እና አዳዲስ ወደ ዘርፉ የመጡ አልሚዎችን ተነሳሽነት ለመጨመር ዓለማ ያደረገው ኢትዮ ሪል እስቴት አዋርድ መዘጋጀቱን አዘጋጁ አርክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ዛሬ ነሃሴ 16/2017 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
ኢትዮ ሪል እስቴት አዋርድ ላይ ለመሳተፍ 20 ያህል አልሚዎች በአርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘርጋር የቅድመ ተሳትፎ ውል የተዋዋሉ ሲሆን በሰሩት እና ባለሙት ልክ ውድድር ሳይሆን እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።
አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ኢትዮ ሪል እስቴት አዋርድን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ተሳትፎ ጋር አዘጋጅቶታል።
የእውቅና መርሃ ግብሩ ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።
#ልዩ_ልዩ




