banner

ፈናን ፔይ የዲጅታል ክፍያ ስርዓት በይፋ ስራ ጀመረ

#FastMereja I በፈናን ፔይ ሶሉሽንስ አክሲዮን ማህበር የበለፀገው ፈናን ፔይ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልቶ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው የዲጅታል ክፍያ ስርዓት በይፋ ሥራ መጀመሩ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ተገልጿል።

ፈናን ፔይ የዲጅታል ክፍያ ስርዓት በአገልግሎት ሰጪዎችና በደንበኞቻቸው መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የመስመር (online/electronic payment) ላይ ግብይቶችን ለማመቻቸት የተነደፈ የክፍያ ዘዴ ነው ተብሏል።

ፈናን ፔይ በባንክ ሥራ ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተመሠረተ ከመሆኑ አንፃር ቴክኖሎጂው አስተማማኝ መሆኑን በተግባር ጭምር ተረጋግጧል ተብሏል።

የፋይናንስ ተቋማት በገንዘብ ዝዉዉር ላይ የሚያስከፍሉትን ከፍተኛ የሆነ ኮሚሽን የሚያስቀር የዲጅታል የክፍያ ስርዓት ፈናን ፔይ ድርጅቶች እስከ 0 በመቶ (ኮሚሽን እንዳይከፍሉ) የሚደረግበትን አሰራር የሚያበረታታ ነው። ይህ ዜሮ በመቶ ኮሚሽን የሚወሰነው ድርጅቶች ባላቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና ብቃት ሲሆን ይህንን ማሳካት ለማይችሉ ተቋማት ሲስተሙ በራሱ በሚሰጠው አማራጮች በድርድር ገበያው ላይ ካለው ኮሚሽን አነስተኛውን የኮሚሽን ክፍያ እንዲከፍሉ በአማራጭነት በማቅረብ ነው ተብሏል።

ፈናን ፔይ ባለፉት ስድስት የሙከራ ወራት ወቅት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የክፍያ ዝውውሮችን በተሳካ ሁኔታ በማድረግ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ማከናወኑ ተነግሯል።

ባለፉት ስድስት የሙከራ ወራት ወቅት በሁሉም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመዘኛ መስፈርቶች ውጤታማ በመሆን የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ሆኖ እንዲያገለግል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እውቅናን አግኝቷል።

#ቢዝነስ #ሳይ_ቴክ





Leave a Comment