0
#FastMereja – አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በግዕዝ ባንክ አ.ማ ፈራሚዎች የተገዛ አክሲዮን ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ መዛወሩን ገለጸ
በአደራጆችና ፈራሚዎች ስምምነት መሰረት የግእዝ ባንክ አ.ማ የምስረታ ሂደቱ ተቋርጦ ለአክሲዮን መግዣ ያዋሉት ገንዘብ ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ለአክሲዮን መግዣ እንዲዉልላቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ተገለጸ፡፡
ባንኩ እንዳስታወቀው በምስረታ ላይ የነበረው ግእዝ ባንክ አ.ማ በአደራጆችና ፈራሚዎች ስምምነት መሰረት የምስረታ ሂደቱ ተቋርጦ ለአክሲዮን መግዣ ያዋሉት ገንዘብ ወደ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ለአክሲዮን መግዣ እንዲዉልላቸዉ ያቀረቡትን ጥያቄ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል ተቀባይነት አግኝቶ በመጽደቁ የግዕዝ ባንክ ፈራሚ ባለአክሲዮኖች ባንኩን መርጠዉ አብረዉ ለመስራት በመፍቀዳቸዉ የተሰማዉን ደስታ ገልጿል፡፡
#ቢዝነስ

4 comments
ሰላም ለኪ
አንበሳ 😎
የትላንት ዜና 😭
እንዲህ ነው በጊዜ ላሽ ማለት!
አርማቸውን የአክሱም ሀውልት ሲሆን ጠርጥሬ ነበር