#FastMereja I ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዓመታዊ የቤተሰብ ቀን ዝግጅት ዛሬ መስከረም 3/2018 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አካሄደ።
የኩባንያው የ2017 የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም በሠራተኞች እውቅና እና ሽልማት የታጀበ ሲሆን፣ የእቅድ ሪፖርት ኮርፖሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አክሊሉ ሙሉጌታ ዝርዝር መረጃዎችን አቅርበዋል።
ግሩፑ ከግብር በፊት ባገኘው ትርፍ ከዕቅዱ 167.5% በላይ በማስመዝገብ እና ካለፈው ዓመት የ134.1% ጭማሪ በማሳየት አስደናቂ ውጤት ማሳየቱ ተገልጿል።
ለሠራተኞች ደመወዝ ብቻ 6.9 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም ለሠራተኞቹ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል።
የምርት ዋጋ አፈጻጸም በ89.7% ሲጨምር፣ ሽያጭ ደግሞ በ112.8% ዕቅዱን አሳክቷል። ከሁሉም ዘርፎች በተለይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከታቀደው በላይ 102% ማከናወኑ ተመላክቷል።
የውጭ ምንዛሪ ገቢ ሚድሮክ በበጀት ዓመቱ 263 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ በማግኘት ከአገሪቱ ኢኮኖሚ ጋር ያለውን ቁርኝት አሳይቷል። ከዚህ ውስጥ 75% የሚሆነው ገቢ የተገኘው ከማዕድን ዘርፍ ነው።
ማኅበራዊ ኃላፊነት ከንግድ ሥራው ጎን ለጎን ለማኅበራዊ አገልግሎቶች 1.1 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ገልጿል። ይህም እንደ ዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎች ግንባታ፣ ለምግብ ማዕከላት እና ለኩላሊት እጥበት ማሽን ግዢ የመሳሰሉ ጠቃሚ ሥራዎችን ያካትታል።
በመሳሪያዎች እርጅና እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት አንዳንድ ችግሮች እንዳጋጠሙት ጠቁሟል። ነገር ግን፣ በቀጣይ ዓመት ምርታማነትንና ትርፋማነትን ለማሳደግ፣ አዲስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና የውስጥ አቅምን በማጠናከር ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ አሳውቋል።
588 ግንባር ቀደም ሰራተኞቹን ከ100 ሺህ ብር እስከ 500 ሺህ ብር ሽልማት አበርክቷል።
#ቢዝነስ




