0 #FastMereja I የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤት ሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የሚድሮክ ቤተሰብ ቀን ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የህዳሴው ግድብ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን፣ ባለፉት 5 አመታት የተሰራው ስራ የሚያኮራ ነው፣ በቀጣይ ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እንጀምራለን ሰራተኞችን እንጨምራለን ብለዋል። ደሃ እንዳይሰቃይ የዋጋ ግሽበትን እንዲቋቋም መስራት ይገባናል ሲሉ ተናግሯል።