banner

ከህመም ጋር እየታገለ የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናውን ያጠናቀቀው ብርቱው “አሉዲን” ጥሩ ውጤት አስመዘገበ

#FastMereja I ተማሪ አሉዲን ሁሴን የበደሌ ኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነው። የ12ኛ ከፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቆ የመፈተኛ ቀኑ ሲደርስ ሕመም ያጋጥመዋል። ተማሪ አሉዲን ህክምና ሂዶ ምርመራ ሲያደርግ የትርፍ አንጀት እንደሚገኝበት በዶክተሮቹ ይነገረዋል።

በዚህ አጋጣሚ ጭንቀት ውስጥ የገባው ጎበዙ ተማሪ ሕመሙ ፈተናውን መጨረስ የሚያስችልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ ት/ቤቱ ከዶክተሮቹ ጋር በመነጋገር መድኃኒት እየወሰደ እንዲፈተን መደረጉን የት/ቤቱ ር/መምህር አቶ ይልማ ገቢሳ በወቅቱ ተናግረዋል።

ህክምና እየተደረገለት ለ3 ቀን ሲሰጥ የነበረውን የማሕበራዊ ሳይንስ ፈተና ያጠናቀቀው ይህ ጎበዝ ተማሪ 472 ማምጣት ችሏል።

መረጃው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ነው



Leave a Comment