0
#FastMereja I “ለምስክርነት የቆየች ህይወት” የተሰኘው በዮድ አቢሲኒያ ባለቤት የቀኝ አዝማች በኩረ ምዕመን ትዛዙ ኮሬ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው።
መፅሐፉ ከልጅነት እስከዛሬ ያሳለፉትን ውጣ ውረድ እና የህይወት ታሪካቸዉን የሚገልፅ መፅሐፍ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን “መስቀረንዳ በቃያንዳ” በሚል መሪ ቃል በዮድ አቢሲኒያ የተዘጋጀው 15ኛው የጉራጌ መስቀል በዓል እና የደንበኞች ቀን በሚከበርበት የፊታችን እሁድ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚመረቀ ተገልጿል።
መጽሐፉ ከ2.1 ሚሊዮን ብር በላይ ሙሉ ወጪው በዮድ
አቢሲኒያ ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተሸፈነ ሲሆን የታተመው 5ሺ ቅጂ መጽሐፍ ሽያጭ ሙሉ ገቢዉ ለተመረጡ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንደሚዉልም ተገልጿል።
የዘንድሮው “መስቀረንዳ በቃያንዳ” ፕሮግራም እንዲህ አይነት የበጎ አድራጎት ስራ የሚከናወንበት ይሆናል የተባለ ሲሆን በዓሉ ዘንድሮ ልዩ ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ተብሏል።
መፅሐፉ 1000 የኢትዮጵያ ብር ለሽያጭ ይቀርባል።
#ልዩ_ልዩ




