#FastMereja – ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማት ለወጣቶች የተሰኘ ፕሮጀክት በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ወጣቶች ተገቢውን ድጋፍ አግኝተው: ሁለንተናዊ ደህነነታቸው ተጠብቆ፣ ራሳቸውን ችለው፣ ብሎም በሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማትና እድገት አስተዋጾ የሚያበረከቱ እንዲሆኑ ጠንካራ ሰብዕናቸውንና እምቅ ችሎታቸውን በማጎልበት ማህበረሰባቸው ዘንድ በጎ አስተዋፅዎ እንዲያበረከቱ የሚያግዝ ኘሮጀክት እንደሆነ የድርጅቱ ብሄራዊ ዳይርክተር አቶ ሣህለማርያም አበበ ገልፀዋል።
ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶችን በተለይም ወጣት ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን በኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ ባለው አረንጓዴ ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያስችላቸውን ከህሎቶችና ድጋፍ በመስጠት የኢኮኖሚ ተሳትፏቸውንና ብርታታቸዉን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።
ይህ ለ5 አመት የሚቆይ ፕሮጀከት በኤሰ ኦ ኤስ የሕጻናት መንደሮች በካናዳ በኩል ከካናዳ መንግስት በተገኘ የ4 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበር ሲሆን ተደራሽ የሚያደርገውም በአዲስ አበባ፣ በአዳማና በድሬደዋ ከልሎች የሚገኙ ከ7,ዐዐዐ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች እንደሚሆንም ተነግሯል።
የፕሮጀክቱ ዋና አላማ ወጣቶች አስፈላጊው ክህሎት ኖሯቸው የሥራ ዕድል እንዲያገኙ፣ የቴከኒክና ሙያ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አቅማቸው ጎልብቶ ጥራት ያለው ትምህርትና ሥልጠና አሰጣጣቸውን እንዲያሻሽሉ እና በራስ መተማመናቸዉ እንዲያድግ ነዉ።
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ፌዴሬሽን ብሄራዊ አባል የሆነዉ ይህ ድርጅት በህጻናት ደህንነት ጥበቃና ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ከማናቸውም ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ እሳቤዎች ገለልተኛ የሆነ አለም አቀፍ የልማት ድርጅት ነው፡፡
ድርጅቱ ከተመሰረተበት እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1966 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ 31 አመታት በህጻናት ወጣቶች, ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ ላይ አምንታዊ ለውጦችን እያመጣ የሚገኝ ድርጅት ነዉ።



