banner

የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ካቴደራል ለ20 ዓመት የሚተገበር የማስተር ፕላን ፕሮጀክቱን አስተዋወቀ

#FastMereja I የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ካቴደራል አጠቃላይ የቦታውን ህጋዊነት ከማረጋገጥ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ክብር በጠበቀ መልኩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመሥራት በከፍተኛ ባለሙያዎች ላለፉት አንድ አመት ሲጠና የነበረው የመሬት ሃብት አጠቃቀም መሪ ዕቅድ ዙሪያ ላይ አስመልክቶ የአካባቢው ማህበረ ምዕመናን ጋር ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ውይይት ተደረገ።

የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ጸሐይ ቀሲስ በቀለ ተሰማ በካቴደራሉ ያለውን ሰፊ ይዞታ ለዘመናዊ ልማት ለማዋል የተነደፈውን የ20 ዓመት የማስተር ፕላን ፕሮጀክት አስመልክቶ በዛሬው እለት የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ገለጻ አድርገዋል።

ካቴደራሉ ከ171 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ በካርታ የተረጋገጠ ሰፊ ይዞታ ያለው ሲሆን፣ ከአምልኮቱ ስፍራ ውጪ ያለው ቦታ በተወሰኑ መጋዘኖች እና ሱቆች የተሸፈኑ የሚገኙ እንደመሆኑ መጠን በዚህ መጠን መቀጠል የለበትም የሚሉት የካቴደራሉ አስተዳዳሪ በአሁኑ ወቅት ከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን በከፍተኛ ሁኔታ እያለማ እያሳደገ በመሆኑ ካቴደራሉ ይህንን መነሻ በማድረግ ትምህርት ቤቶችን ኮሌጆችን ዩኒቨርሲቲዎችን ማሰልጠኛዎችን የመሳሰሉትን ሌሎችም ምግባረ ሰናይ መፈጸሚያ ስፍራዎችን በመስራት ለማህበረሰብም ተደራሽ በሆነ መልኩ ለአገልጋዩ ካህናትም የኑሮ መደጎሚያ የሚሆን ነገር መስራት ስለሚገባ ካቴደራሉ ባላው ይዞታ ላይ የተሻለ ስራ ለመስራት ለአንድ አመት ያህል በይዞታው ላይ ተገቢው ከከተማው አስተዳደሩ ማስተር ፕላን ጋራ ተመጣጣኝ የሆነ ፕላን በማሰራት ወደ ተግባር መግባት የሚያስችለውን የቅድመ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

የማስተር ኘላን ኘሮጀክቱ ወደ መሬት ሲወርድ ቅድሚያ ተሰጥቶተት የሚሰራው የካቴደራሉን ይዞታውን ማስከበር እና ለአምልኮ ስፍራውን ምቹ ማድረግ ፣ ካቴደራሉ ከአራቱም ማዕዘን ለየት ባለ መልኩ እንዲታይ ማድረግ ፣ የካቴደራሉ ቅጽረ ግቢ ውብ እና ለጸሎት ምቹ ማድረግ የመጀመሪያ ስራ ሲሆን

ሁለተኛው ምዕራፍ ላይ መካነ መቃብሩን ማስተካከል እና ማስዋብ። አሁን አምስት ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የማጽናት፣ የማስዋብ እና የማጠር ስራ መሰራቱን መልአከ ጸሐይ በቀለ ተሰማ ገልጸዋል።

በቀጣይ 20 አመታት ትምህርት ቤቶችን እና ሌሎች ማሰልጠኛዎችን በቅደም ተከተል እንደሚገነባ ገልጸዋል።

መልአከ ጸሐይ ቀሲስ በቀለ ተሰማ በመጨረሻ ባስተላለፉት መልዕክት በውጭም አገር እና በሀገር ውስጥ ለሚኖሩ የአጥቢያው ማህበረ ምዕመናን ፣ ካህናት የመጀመሪያው የምንፈልገው እውቀት ነው። እውቀት ነው ገንዘብን ሀብትን ማስተዳደር የሚችለው ስራዎችን መስራት የሚችለው እና ምዕመናን እውቀታቸውን በዚህ በቅርብ ያሉ በአጥቢያው ያሉ ምዕመናን በእውቀት መጀመሪያ እንዲያግዙን አረጋውያን በጸሎታቸው ካህናት በጸሎታቸው እንዲደግፉን እንፈልጋለን ያሉ ሲሆን በሌላው ክፍለ ዓለም ያሉ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳጆች በሙሉ የአጥቢያው ተወላጆች በሌላው ክፍለ ዓለም ያሉ ሁሉም የቅድስት ቤተክርስቲያን ወዳጆች በገንዘባቸው በጸሎታቸው በእውቀታቸው እንዲያግዙን ከዚህም ባሻገር ባለሀብቶች ባንኮች ኢንሹራንሶች ሌሎችም ከቤተክርስቲያኗ ጋራ በመሆን በጋራ ቦታችንን ለማልማት እኛ በይዞታ እነሱ ደግሞ በሀብት እንዲያግዙን እና በጋራ እንስራ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።





Leave a Comment