0
#FastMereja I 11ኛውን የጉማ ፊልም ተዋናይት ወለላ አሰፋ እና ተዋናይት ፍቅርተ ጌታሁን የሕይወት ዘመን ተሸላሚ አድርጎ እንደሚሸልም እንዲሁም የዛሬ 50 ዓመት ወ/ት አዲስአበባ ተብላ የተሸለመችው ወሰኔ ኃይሉ የጉማ ሔርሜላ ተሸላሚ መሆኗ ይፋ አደረገ።
የጉማ አዋርድ አዘጋጆቹ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ሽልማቱ በአድዋ ሙዚየም ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይከናወናል።
በዕለቱ አለባበስ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠውና የሀገር ባህል አልባሳት እንጂ እርቃንን የሚያሳይ አለባበስ እንደማይፈቀድ አቶ ዮናስ ብርሃነ መዋ አስረድተዋል።
በተጨማሪም ኀብረተሰቡን ለማሳተፍ የተወሰነ ቲኬት በሽያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚቀርብ ተነግሯል። የሽልማት ካታጎሪው ዘንድሮ ቀንሶ ወደ 20 እንዲወርድ መደረጉን ገልፀው የዘንድሮ ሽልማት በአድዋ 130ኛ ዓመት የሚከበርበት ዓመት መሰጠቱ ልዩ እንደሚያደርገው ተጠቅሷል።
ዘንድሮ ዋና ስፖንሰር ባለፉት 10 ዓመታት አብሮ የተጓዘው በደሌ ቢራ ሲሆን አሪፍ ፔይ እና ኢትዮፒካር አዳዲስ ስፖንሰሮች መሆናቸው ተገልጿል።
#ኪነ_ጥበብ




