#FastMereja I የኢትዮጵያ አጥንት ህክምና ሃኪሞች ማህበር ለ18ኛ ጊዜ “በመረጃ የተደገፈ ዘመናዊ የአጥንት ህክምና በማድረስ ክፍተትን መሙላት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 8 እስከ 9/2018 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ጉባኤዉን ማካሄድ ደምሯል።
በዚህ ጉባኤ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እንዲሁም በዘርፉ የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰሩ ከ500 ያላነሱ ባለሙያዎች ተገኝቷል።
ከስብራት ጋር በተያያዘ በአደጋዉ ተጎጂዎች ማግኘት ስላለባቸዉ ህክምና እና አገልግሎት ምን መሆን እንዳለበት እና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ባለሙያዎች ጋር የተለያዩ ልምድ ልዉዉጥ እንደሚኖር ተነግሯል።
በዛሬዉ ጉባዔም በማህበሩ የተከናወኑ ጥናታዊና የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲሁም ለአጥንት ህክምና የሚውሉ የህክምና መሳሪያዎች እና ሌሎች ግብአቶችን የሚያቀርቡ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ለእይታ ያቀረቡበት ኤግዚቢሽንም ተከፍቶ ለእንግዶችና ለተሳታፊዎች ክፍት ሆኖ እየተጎበኘ ነው።
በማህበሩ ውስጥ በአጥንት ህክምናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አሁንም እያበረከቱ ለሚገኙ ከተለያዩ ሀገራት ለመጡ የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም ተቋማት የምስጋና እና የዕውቅና ሽልማት ተበርክቷል።
ይህ የህክምና ማህበር ከተቋቋመ ግንቦት 1995 ዓም ሲሆን በዚህ ሰአት ከ695 በላይ ማህበራትን የያዘ ማህበር መሆኑ ተገልጿል።
#ኹነት #ጤና




