#FastMereja I የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሎሽንስ ጋር በመሆን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አሸናፊዎችን በታላቅ ስነ-ስርዓት በዛሬዉ እለት ሸለመ።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ለ65 ዓመታት ያህል ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የደስታ እንዲሁም የለውጥና የዕድል ምንጭ ሆኖ አገልግሏል ሲሉ ገልፀዋል::
የሽልማት መጠኑን በ50 ሺህ ብር አሀዱ ብሎ ጀምሮ ዛሬ ላይ ሽልማቱን በሚሊዮን አሳድጎ በርካቶችን በሽልማት ያንበሸበሸ ትልቅ ተቋም መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር ባሳለፉት ዓመት አራት የሎተሪ ዘመቻን በዲጂታል በመሸጥ በስኬት አጠናቋል።
ለሁለት ወራት ያህል በዲጂታል እና በወረቀት ሲሽጥ የቆየው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ታላላቅ የገንዘብ ሽልማቶች በዲጂታል እና በወረቀት ለገዙ 20 ሚሊዮን ብር፣ 10 ሚሊዮን ብር፣ 5 ሚሊዮን ብር፣ 2 ሚሊዮን ብር እና በርካታ የገንዘብ ሽልማቶች ለባለዕድለኛ ተበርክቷል።
እንቁጣጣሽ ሎተሪን በዲጂታል ለቆረጡ ብቻ ልዩ የቦነስ ሽልማት፡- የBYD ተሽከርካሪ እና የኤሌክትሪክ ባጃጅ ለዕድለኞች ሽልማታቸዉን ተረክበዋል።
አሁን ላይ ይህ ተቋም ከዘመኑ ጋርእኩል በመራመድ በቴክኖሎጂው እየታገዘ ሎተሪን በወረቀት ብቻ ሳይሆን በዲጂታል አማራጭ በማቅረብ ደንበኞቹ በየትኛውም ቦታ ሆነው በቀላሉ ዕድላቸውን እንዲሞክሩ አስችሏል ተብሏል።




