#FastMereja I ሞዴል ሌንሳ ጥላሁን ነዋሪነቷን በአሜሪካን ሃገር ያደረገች ትውልደ ኢትዮጵያዊት የቢዝነስ ሰው ስትሆን ከዚህ ቀደም በሚስ ኢትዮጵያ ውድድር ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን የሚስ ኦሮሚያ የቁንጂና ውድድርን ደግሞ በአንደኝነት በማሸነፍ ሃገሯን በአለም አደባባይ ያስጠራች ኢንተርናሽናል ሞዴል ናት ።
ኮኬት ኢንቨስትመንት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 የተቋቋመ ሲሆን በዋነኛነት በሶፍት ዌር ኢንጂነሪንግ ፣ በሶፍት ዌር ማበልፀግና ለተቋማት ማቅረብ ፣ በኮንስትራክሽን እና በኢንቴሪየር ዲዛይ ስራ ላይ የተሰማራ ሃገር በቀል ድርጂት ነው ።
ኮኬት ኢንቨስትመንት ኢንተርናሽናል ሞዴል ሌንሳ ጥላሁንን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ የሾማት ድርጂቱ የሚሰጠውን አገልግሎት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ተደራሽ ለማድረግ ሞዴል ሌንሳ አሜሪካንን ጨምሮ በተለያዮ የአለም ሃገራት ካካበተችው አለም አቀፍ እውቅናና የስራ ተነሳሽነት እንደዚሁም ኮኬት በቀጣይ አለማቀፍ የቢዝነስ ሰዎች ጋር ለሚያደርገው ግንኙነት ራዕዮን እውን ከማድረግ አኳያ ስኬታማ ተግባራትን እንደምታከናውን በማመን መሆኑን የኮኬት ኢንቨስትመንት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዋሲሁን ተፈራ ገልፀዋል ።
ኢንተርናሽናል ሞዴል ሌንሳ ጥላሁን የኮኬት ብራንድ አምባሳደር ለመሆን 15 ሚሊየን ብር የተከፈላት ሲሆን ኮኬት ኢንቨስትመንት ከሃገር አልፎ በተለያዮ የአለም ሃገራት ለሚያደርገው የንግድ እና የተለያዮ አገልግሎቶች እንቅስቃሴ የተቋሙን ርዕይ እውን ለማድረግ እንደምትሰራ ቃል ገብታለች ።





6 comments
Ere fetari inenim iyegna please
Dembi dollo 💪💪
ይመቻት
ያጣፍጥላት🙌
ርቦናል ቸግሮናል
Congratulations Lensa Tilahun