banner

ኢንፊኒክስ ሞባይልና የአዲስ አበባ ተግባረኢድ ኮሌጅ አብረዉ ለመስራት ተፈራረሙ።

#FastMereja I ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ተግባረ-ኢድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወጣቱን በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመደገፍ እና አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት (MOU) በዛሬዉ እለት ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም አከናዉኗል።

የመግባቢያ ስምምነቱ የኢንፊኒክስ ክለብን በተግባረ ኢድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያቋቁማል፣ ይህም ለተማሪዎች ለተግባራዊ የኢንዱስትሪ ልምድ፣ ለክህሎት ግንባታ እና ለፈጠራ ፍለጋ እድሎችን ይሰጣልም ተብሏል፡፡

የሁለቱ ትብብር ለተማሪዎች የአካዳሚክ ትምህርትን ከሙያዊ ልምድ ጋር የሚያገናኙ የኢንዱስትሪ ግንዛቤዎችን፣ መመሪያዎችን እና ስልጠናዎችን እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

የኢንፊኒክስ ቀን ደንበኞችን ከተለያዩ የኢንፊኒክስ ምርቶች ጋር ለማስተዋወቅ እና በአዲሶቹ ቴክኖሎጂዎች የተግባር ልምድ ለማቅረብ ያለመ ወርሃዊ ዝግጅት 6ኛውን የኢንፊኒክስ ቀንን አከብሯል።

በዚህ ልዩ ክብረ በዓል ሙዚቃን፤ ካራኦኬን እና የተለያዩ ምርቶችን አሳይቷል፣ ይህም ለተማሪዎች እና ለእንግዶች አስደሳች እና አስተማሪ ድባብ እንዲፈጠር አድርጓል። የኢንፊኒከስ ተወካዮች በብራንዱ ዲጂታል መድረኮች ላይ ለተደረጉ ለተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ውድድሮች አሸናፊዎችንም ሽልማቶችን አበርከቷል።





Leave a Comment