banner

አሲዳማ መሬት በኖራ እየታከመ ከፍተኛ ምርት እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ

#FastMereja I የአፈር አሲዳማነትን በማከም የአፈሩን ጤንነት በመጠበቅ በዘላቂነት የግብርናውን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን የግብርና ኖራ ግብዓትን በመጠቀም እንደሀገር የልምድ ልውውጥና ምርጥ ተሞክሮ ለመቀመር እና ለማስፋት ግሪን ዌቭ አሊያንስ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በወልመራ ወረዳ በተመረጡ ቀበሌዎች ከፍተኛ አመራር እና በመሪ ስራ አስፈጻሚዎች፤ የፕሮግራምና ፕሮጀክት ማኔጀሮች እንዲሁም የክልሎች የዘርፍ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በተገኙበት የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

በኩታ ገጠም እና በክላስተር የታረሱ በኖር የታከሙ መሬቶች ከዚህ ቀደም ከሚሰጡት የምርት መጠን በእጥፍ እየሰጡ እንደሆነ በመስክ ምልከታው ወቅት ማበራሪያ ተሰጥቷል።

ተሞክሮ ውጤታማ በመሆኑ በሌሎች አከባቢዎች በማስፋት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

አሁን እየተዘራ የሚገኘው ጥራቱን የጠበቀ የቢራ ገብስ በመሆኑ በአቅራቢያው የሚገኘው ኬኛ ቢራ እየተረከበ ሲሆን በቀጣይ ከድንች ጋር እየተፈራረቀ በኖራ የታከመው መሬት ከፍተኛ ምርት እየሰጠ እንደሚገኘ ተነግሯል።

ግሪን ዌቭ አሊያንስ በአርቲስት ሚኪያስ ነጋሳ የተመሰረተ ሲሆን ባለፉት ዓመታት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን የኪነጥበብ እና የሚድያ ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የማኀበረሰብ ክፍሎችን በማንቀሳቀስ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ሲካኼድ የቆየ ድርጅት ነው።





Leave a Comment