banner

“መልቲ” ትያትር በአዲስ መልክ ለዕይታ ሊበቃ ነው።

#FastMereja I በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ታሪኩን ማጠንጠኛ ያደረገው መልቲ ትያትር ከአመታት በፊት በአዲስ አበባ ቴአተርና ባህል አዳራሽ-ማዘጋጃ ቤት ለዕይታ በቅቶ የነበረ ትያትር ነው።

ትያትሩ ዘመኑን በሚመጥንና በአዳዲስ ሀሳቦች ዳግም እንደተዘጋጀ ዛሬ ሕዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።

ምትኩ በቀለ፣ ኤልሻዳይ ከበደ፣ ሱራፌል ብስራት፣ ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው፣ አቤል ሰለሞን እና ሰላማዊት ካሳዬ በትወና የተሳተፉ ሲሆን በመልቲ የትያትር ቡድን ተደርሶ በስንታየሁ ታዬ (ፋቡላ) ተዘጋጅቷል።

የኮሜዲ ዘውግ ያለው “መልቲ” ቴአትር የትያትር ወዳጆችን እርካታ ለመሙላት በማሰብ ከፍ ባለ ሙያዊ ጥንቃቄ ለአንድ አመት ያህል በተዋንያን መረጣ፣ አልባሳትና መሰል ሙያዊ ዝግጅቶች ላይ መቆየቱ ተነግሯል።

ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው ታላላቅ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የትያትርና ፊልም መምህራን ብሎም የተመረጡ እንግዶች በተገኙበት በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ይመረቃል።

ከምርቃቱ በኋላም ዘወትር አርብ በ12:00 ሰዓት ብስራተ ገብርኤል በሚገኘው አዶት ሲኒማ መታየት ይጀምራል።

የትያትር ተመልካቾች የቴአትር ቤት መግቢያ ትኬታቸውን በእናት ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ሲስተም መቁረጥ የሚያስችላቸውን አሰራር በዕለቱ ይፋ ሆኗል።

በዚህ አሰራር መሰረት ትያትር ተመልካቾች የመግቢያ ትኬታቸውን በእናት ባንክ ዲጂታል ባንኪንግ አማካኝነት በቀላሉ መቁረጥ የሚችሉ ይሆናል።

ይህንን አሰራር ለመጀመሪያ ጊዜ አዶት ሲኒማ ከእናት ባንክ እና ከመልቲ የትያትር ቡድን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ በመፈራረም ያስጀመሩ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች ትያትር እና ሲኒማ ቤቶች አሰራሩ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።

#ኪነ_ጥበብ ዘገባ





Leave a Comment