#FastMereja I ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት እ.ኤ.አ 2016 ዓ.ም በዶክተር ፅጌ ጥበቡ አማካኝነት በኢትዮጵያ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ አለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን የአእምሮ እድገት ውስንነትና ሌሎች የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህፃናትና ወጣቶች በመንፈሳዊ ስሜታዊ ትምህርታዊና ሙያዊ ፕሮግራሞች በመደገፍ በክብርና በነፃነት እንዲማሩ እንዲሰሩና እንዲኖሩ የሚያስችል ከባቢን ለመፍጠር እየሰራ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ነዉ።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ወጣቶች በሸማ ሙያ፣ በኮምፒውተር (ኮዲንግ) በሙዚቃ, በሥነ ሥዕል በስፖርት እና በሌሎችም ዘርፎች 1300 በላይ ተጠቃሚዎችን በማሰልጠን እንዲሁም የሕክምናና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን እየሠደረገ ይገኛል።
ለትምህርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ራዕይ የህፃናት መርጃ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለተመዘገቡ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁሶችን ያቀርባል። እስካሁን 126 ተማሪዎችን ደግፏል።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ዓላማው ልጆችን በትምህርት ቤት ለመወጣት ጠንካራ ሙያዎችን ለማዳበር እና የማህበረሰባቸው ንቁ አባላት እንዲሆኑ የሚያስፈልጋቸውን ችሎታዎች ለማጉላት እንዲያግዝ አትሌት መሰረት ደፋርን ብራንድ አንባሳደር አድርጎ ሾሟል።
በህብረተሰባችን ውስጥ ችላ ከተባሉ ልጆች ጋር በመስራት ራዕይ የህፃናት መርጃ የወደፊት ህይወታቸውን ከፍ ለማድረግ እና ለህይወታቸው አዎንታዊ እይታን ለመስጠት ብዙ ስራዎችን እንደምትሰራም አትሌት መሰረት ደፋር ገልፃለች።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ዓላማው ልጆች በትምህርት ቤት ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስፈልጋቸውን ችሎታዎች ለማስታጠቅ ጠንካራ ሙያዎችን ለማዳበር እና የማኅበረሰባቸው-ግንኙነታቸው ንቁ አባላት እንዲሆኑ ማድረግ እንደሆነ እና በዚህ በጎ አድራጎት ስራ ላይ እነዚህን ህፃናት በመደገፍ እና ህይወታቸዉ ላይ ለዉጥ ለማምጣት ህብረተሰቡ እንዲቀላቀል የድርጅቱ መስራች ዶ/ር ፅጌ ጥበቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት በበዛሬው እለትም ድጋፍ ከሚያደርግባቸው ት/ት ቤቶች ውስጥ በትንቢተ ኤርሚያስና በስብስቴ ነጋሲ ት/ቤቶች የሚማሩ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች የሚሰሯቸውን የሙያ ስራዎች እንዲሁም ህፃናቱን ያሉበትን ሁኔታ በአካል በመገኘት ጉብኝት አካሂዷል።




